ዳቦ እና እንጀራን በየሰፈሩ በሚገኙ የሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ መደብሮች እንዳይሸጡ በህግ የተከለከለው ከ7 ዓመት በፊት ቢሆንም ክልከላው የተላለፈው ከሰሞኑ ነው
TRACK

ዳቦ እና እንጀራን በየሰፈሩ በሚገኙ የሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ መደብሮች እንዳይሸጡ በህግ የተከለከለው ከ7 ዓመት በፊት ቢሆንም ክልከላው የተላለፈው ከሰሞኑ ነው

Avatar

ህዳር 12 2018

ዳቦ እና እንጀራን በየሰፈሩ በሚገኙ የሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ መደብሮች እንዳይሸጡ በህግ የተከለከለው ከ7 ዓመት በፊት ቢሆንም ክልከላው የተላለፈው ከሰሞኑ ነው፡፡

አዋጁን ለማስፈፀም ለምን እስከ አሁን ዘገያችሁ ስንል የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለ ስልጣንን ጠይቀናል፡፡

ከሰሞኑ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በየመንደሩ ያሉ የሸቀጣሸቀጥ መደብሮች ዳቦና እንጀራን እንዳይሸጡ ቢከለክልም መደብሮቹ ዳቦውንም ይሁን እንጀራውን ከመሸጥ አልተቆጠቡም፡፡

ውሳኔውን በሚተላለፉ ነጋዴዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ እንደምን ያለ ነው? ስንል ጠይቀናል፡፡

የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ወደዚህ እርምጃ እንዲገባ ምክንያት የሆነው በየሱቁ የሚሸጡ እንደ ዳቦ እና እንጀራ ያሉ የበሰሉ ምግቦች ከአቀማመጥ አንፃር እየተበከሉ፣ ለማህበረሰቡም የጤና ጠንቅ እየሆኑ መምጣታቸውን በመረዳት ነው ብሎናል፡፡

Comments

Avatar