00:00
ሚያዝያ 8 2017
‘’የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ባሰራጨው መረጃ ምክንያት የኦዲተርነት ሙያ ላይ ስም ማጥፋት ተፈፅሟል፣ የባለሞያዎቹን ተዓማኒነት በማሳጣቱ ሞያዊ ኪሳራ አድርሷል’’ ያሉ የሙያ ማህበራት ቢሮው ጉዳዩን እንዲያስተባብል ጠይቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የገቢ ግብርን በማሳነስና በመሰወር የተሳሳተ የሂሳብ ሪፖርት አቅርበውልኛል እርምጃ ይወሰድባቸው ብሎ በሚዲያ ያስተላለፈው መረጃ የኦዲተርነት ሙያን ከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ መክተቱን 3 የሂሳብና የኦዲተሮች ማህበራት ተናግረዋል።
በቅርቡ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ከወንኩት ባለው የቅድመ ኦዲት ስራ ባለፈው ዓመት ብቻ 36,729 የታክስ መዝገቦች ገቢ በማሳነስና በመሰወር የሚቀርቡ መሆናቸውን ደርሼበታለሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሂሳብ እና የኦዲት ቦርድ ፈቃድ ከተሰጣቸው 863 የሂሳብ ባለሙሞያዎችና ኦዲተሮች 824ቱ ባለሞያዎች ያቀረቡት የሂሳብ ሪፖርት በማሳነስና በመሰወር የቀረበ በመሆኑ፤ በቦርዱ ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ፍቃድ መንጠቅ የደረሰ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ቢሮው መጠየቁን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።
Comments
00:00