ሰኔ 20፣ 2016
የክልል መንግስታት በክልላቸው እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎችን ራሳቸውን ችለው እንዲረዱ ተነግሯቸዋል ተባለ፡፡
ሚሊዮኖች በተፈናቀሉበት ሀገር የፌዴራሉ መንግስት እርዳታን በተመለከተ እጁን ለማውጣት ለምን ፈለገ?
ችግሩ ክልሎች ለብቻቸው የሚወጡት ነው ወይ?
በድርቅና በፀጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን የያዙ ክልሎች እንዳሉ ይታወቃል፡፡
እነዚህ ክልሎች እንኳን በራሳቸው ድጋፍ አቅርበው ችግረኞችን ሊረዱ ይቅርና የፌደራል መንግስት እያገዛቸው አለማቀፍ የረድኤት ድርጅቶችም እያቀረቡ እርዳታው አሁንም በቂ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ መናገራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ታዲያ ክልሎች በራሳቸው ብቻ ይቻሉት ከተባለ ችግሩን አያከብደውም ወይ?
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…
ማርታ በቀለ
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments