ህገ መንግስቱን ይቃረናል የሚል የሰላ ትችት የቀረበበት የአጠቃላይ የትምህርት አዋጅን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፅድቆታል
TRACK

ህገ መንግስቱን ይቃረናል የሚል የሰላ ትችት የቀረበበት የአጠቃላይ የትምህርት አዋጅን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፅድቆታል

00:00

ጥር 22 2017

የሀገሪቱ ህጎች ሁሉ የበላይ ነው የሚባለው ህገ መንግስቱን ይቃረናል የሚል የሰላ ትችት የቀረበበት የአጠቃላይ የትምህርት አዋጅን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አፅድቆታል፡፡

ምክር ቤቱ ያጸደቀው አጠቃላይ የትምህርት አዋጅ የምክር ቤት አባላት ህገ መንግስቱን ይቃረናል ሲሉ ተችተውታል፡፡

የምክር ቤቱ አባል ደሳለኝ ጫኔ(ዶ/ር) አዋጁ የአንድ መግባቢያ የሀገራዊን ቋንቋ አስፈላጊነት የዘነጋን ይመስለኛል ብለዋል፡፡

ህፃናትን በአፍ መፍቻቸው ቋንቋ ማስተማር መሰረታዊ የህፃናት መብት መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ደሳለኝ ህፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የማስተማር አስፈላጊነት ያክል ደግሞ አንድ አስተሳሳሪ የሆነ ሀገራዊ ቋንቋ አስፈላጊነት መርሳት የለብንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የ1986 የትምህርት እና ስልጠና ፖሊሲ አማርኛ ቋንቋ በመላ ሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች እንደ አንድ የትምህርት አይነት መስጠትን ይፈቅድ ነበር፡፡

Comments

00:00

Gebku

Go ahead

There is no more content to load