ግብርን የሚያሸሹ ተቋማትን ግብር ማስከፈል እንደቻለ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ተናገረ
TRACK

ግብርን የሚያሸሹ ተቋማትን ግብር ማስከፈል እንደቻለ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ተናገረ

00:00

ጥር 20 2017

በአዲስ አበባ ከተማ ያሉና ከዚህ ቀደም ግብር የማይከፍሉ እንዲሁም ግብርን የሚያሸሹ ተቋማትን ግብር ማስከፈል እንደቻለ የገቢዎች ቢሮ ተናገረ፡፡

ቢሮው በመንፈቅ ጊዜ ውስጥ 111 ቢሊዮን ብር ከገቢ ግብር መሰብሰቡንም ነግሮናል፡፡

በአዲስ አበባ ያሉ ከ119 በላይ ኤምባሲዎች አብዛኞቹ የግለሰብ ቤት የሚከራዩ ናቸው ይሁንና እስካሁን የአከራይ ተከራይ ግብርን አይከፍሉም ነበር አሁን ግን ማስከፈል ጀምሪያለሁ ብሏል፡፡

ከፍተኛ መጠን ያለውን ግብር ያሸሹ የነበሩ ሞሎችን፣ ልኳንዳ ቤቶችንና ሌላውንም ወደ ግብር ስርዓቱ አምጥተናል ያሉን በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ሰውነት አየለ ናቸው፡፡

እንደ ሃላፊው ገለፃ ገቢው ከተማዋ ከምታመነጨው አንፃር አነስተኛ ይሁን እንጂ የተሰበሰበው የ111.6 ቢሊዮን ብር ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ26 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው ለገቢው መጨመር ሌላው ምክንያት መርካቶችነ ጨምሮ በከተማዋ የተጀመረው የደረሰኝ ቁጥጥር ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው ብለዋል፡፡

Comments

00:00