ጥቅምት 19፣2017
‘’በግጭት፣ በጦርነት፣ በተፈጥሮ አደጋ ዋነኛ ተፈናቃይ የሆኑት ሴቶች፣ ህፃናት እና አረጋዊያን አስፈላጊ ድጋፍም እየቀረበላቸው አይደለም’' ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡
በዚህም እነዚህ ሰዎች ለተደራራቢ ችግር ተጋላጭ እንዳደረጋቸው፤ በኮሚሽኑ የሴቶች፣ ህጻናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገ/ሀዋሪያ ለሸገር ራዲዮ አስረድተዋል፡፡
ከነበሩበት ቀዩ ለቀው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከገቡም በኃላ የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እንደሚፈፀምባቸው ኢሰመኮ ጠቅሷል፡፡
ለወለዱ ሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኛ፣ ለህፃናት እና ለአረጋዊያን የሚደረገው ድጋፍ እጅግ አነስተኛ ነው ሲልም ተናግሯል፡፡
ህፃናት ልጆች የትምህርት ጊዜአቸውን በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንዲያሳልፉ ይገደዳሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡
Comments