በዋግህምራ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ 29 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል
TRACK

በዋግህምራ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ 29 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል

Avatar

መስከረም 8፣2017

ባለፉት 3 አመታት ዝናብ ጠብ ባለማለቱ በድርቅ ሲፈተን የቆየው የዋግህምራ ዞን በ2016 የክረምት ወቅት ዝናብ ቢያገኝም በአንዳንድ የዞኑ አካባቢዎች ከፍተኛ ዝናብ በማጋጠሙ ምክንያት ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል ተባለ፡፡

በዞኑ አንዳንድ ወረዳዎች ከፍተኛ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ ጎርፍ እንደተከሰተ የተነገረ ሲሆን በመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ 29 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በደራሽ ጎርፍ ከ400 በላይ እንሰሳት ሲሞቱ 195 የሚሆኑ የአርሷ አደር ቤቶች በላያቸው ላይ መፍረሱን ሸገር ራዲዮ ሰምቷል፡፡

ሸገር ይህንን የሰማው ከዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ነው፡፡

Comments

Avatar