የካቲት 24 2017  -  የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ
TRACK

የካቲት 24 2017 - የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ

00:00

የካቲት 24 2017

በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ በዝሆኖችና በሰዎች መካከል ያለውን ግጭት ሊቀርፍ የሚችል ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው ቢያቀርብም ችግሩ አሁንም ድረስ መፈታት እንዳልቻለ ሲድ አክት የተባለው አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራ ተቋም ተናፍሯል፡፡

በኢትዮጵያ የቱሪስት መስህብ ከሆኑና ዝሆኖች የሚገኙባቸው ስፍራዎች መካከል ትልቁ የሆነውና ከ300 በላይ ዝሆኖች እንደሚገኙበት የሚነገርለት የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ለእርሻ መሬትና ለግጦሽ በሚል በህገወጥ መንገድ በሚያደርጉት ሰፈራ በሚፈጠር ግጭት በሰዎች እና በዝሆኖቹ ላይ ለሞት የሚያበቃ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል፡፡

በተለይ ባለፈው ዓመት የዝሆኖቹ መጠለያ የሆነ 200 ሄክታር የሚሸፍን መሬት ለኢንቨስትመንት በሚል መሰጠቱን ተከትሎ ችግሮች ተባብሰው ዝሆኖቹ በመቆጣት 4 ሰዎችን ገድለዋል፤በዚሁም ወቅት 5 ዝሆኖች መሞታቸውን የመጠለያው አስተዳደር መናገሩ ይታወሳል፡፡

Comments

00:00