ግሎባል ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር 30 በመቶ ለቆጠቡ አባላቱ የኤሌክትሪክ መኪኖችን አስረክቧል
TRACK

ግሎባል ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር 30 በመቶ ለቆጠቡ አባላቱ የኤሌክትሪክ መኪኖችን አስረክቧል

00:00

ግሎባል ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር 30 በመቶ ለቆጠቡ አባላቱ የኤሌክትሪክ መኪኖችን አስረክቧል።

ማህበሩ የአንዱ ዋጋ 2.8 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ተሸከርካሪን 30 በመቶ ማለትም 840 ሺህ ብር ለቆጠቡ 12 አባላቱ ነው በትናንትናው ዕለት ያስረከበው፡፡

የኤሌትሪክ መኪኖችን ከሚያስመጣው ኢትዮፒካር ከተባለው ድርጅት ጋር ውል በማሰር እነዚህን ጨምሮ በየወሩ 100 መኪኖችን ለቆጠቡ አባላቱ እንደሚያስረክብ የነገሩን ግሎባል ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ስራ አስኪያጅ ሞላ ባዘዘው ናቸው፡፡

ተሸከርካሪውን የተረከቡት አባላት የሚቀርባቸውን 70 በመቶ ክፍያ በ14 በመቶ ወለድ እስከ 5 ዓመት ከፍለው ለመጨረስ መስማማታቸውን የሚናገሩት ሃላፊው፣ የኤልክትሪክ መኪኖች መለዋለጫዎች በሃገር ውስጥ እንደልብ የማይገኙ በመሆኑ ይህንን ችግር ለመፍታት ከአስመጪ ድርጅቱ ጋር በመሆን መለዋወጫዎችን ከውጭ እያስመጣን ነው ብለዋል፡፡

የኤሌክትሪክ ተሸከርካራች ባትሪዎች ዋጋ ኪስን የሚፈትን በመሆኑ አባላቱ ለባትሪ መለዋወጫ ተጨማሪ እንዲቆጥቡ እያደረጉ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

Comments

00:00