TRACK
በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በከፍተኛ ት/ት ተቋማት የሚገኙ ወጣቶች ለኤችአይቪ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የኮንዶም አቅርቦትና ግንዛቤው ላይ መሰራት አለበት ተባለ፡፡
መጋቢት 24/2018
በኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የሚገኙ ወጣቶች ለኤች አይ ቪ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የኮንዶም አቅርቦትና ግንዛቤው ላይ መሰራት አለበት ተባለ፡፡
በስራቸው እና ዕድሜያቸው ምክንያት ለኤች አይ ቪ እጅግ ተጋላጭ ከሆኑት ውስጥ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ወጣቶች በተለይ ሴቶች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
ለዚህም የጤና ሚኒስቴር ከለጋሽ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን #ኮንዶም በነፃ እያቀረበ መሆኑን ነገር ግን ይህም ቢሆን በቂ አለመሆኑን ተናግሯል፡፡
በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ያደታ እንደሚናገሩት በተለይ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ተቀጥረው ከሚሰሩት ውስጥ አብዛኛዎቹ ወጣቶች በመሆናቸው የኤች አይ ቪ ተጋላጭነታቸውን መቀነስ ላይ ይበልጥ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
Comments