አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ይሆን?
TRACK

አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ይሆን?

Avatar

ሰኔ 10 2017

ምርጫ ቦርድ ሰባተኛው ሀገራዊ የምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ማድረግ መጀመሩን መናገሩ ይታወሳል፡፡

ለመሆኑ አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ይሆን? ክልላዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በዚህ ጉዳይ ጠይቀናቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ፓርቲ ዋና ጸሓፊው አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ምርጫ በባህሪው ሰላምን ስለሚፈልግ የሀገሪቷን ሰላም ከምርጫ በፊት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

ምርጫ በራሱ ለግጭት በር ከፋች ስለሆነ ከምርጫ በፊት ሰላምን ማስፈን እንደሚያስፈልግ አቶ ዋሲሁን ተናግረዋል፡፡

የባሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር መብራቱ ማሴቦ በበኩላቸው ምርጫ ቦርድ የምርጫ ዝግጅት ማድረግ መጀመሩን ጠቁመው እስከ ምርጫው ድረስ የተወሰነ ጊዜ ስላለ ሰላም ላይ መስራት አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ህብረት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መስኡድ ገበየሁ በበኩላቸው ይህ ጊዜ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲቪል ማህበራት ምርጫ ቦርድና መንግስት በርካታ ዝግጅት የሚያደርጉበት ወቅት እንደሆነ ጠቁመዋል፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምርጫ ሰላም መሰረታዊ ነገር ስለሆነ በቅድሚያ መንግስት ሰላም ላይ እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡

Comments

Avatar