ታህሳስ 11፣2017
በቀደሙት ጊዜአት የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት ክፍተት እንዳለበት ሲነገር ቆይቷል፡፡
ከዚህ ቀደም ዘርፉ እያስተናገደ ነው የሚባለውን ችግር ይፈታል የተባለ አዲስ ስርዓተ ትምህርት ተቀርፆ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡
በ2015 ዓ.ም ቅድመ አንደኛ ተማሪዎች ላይ ሙሉ ለሙሉ ወደ ትግበራ ሲገባ 1ኛ እና 2ተኛ ደረጃ ላይ ደግሞ በሙከራ ደረጃ ሲተገበር እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ ገብቶ የመማር ማስተማሩ ቀጥሎ ቆይቷል፡፡
ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ከቀደመው ሥርዓተ ትምህርት ቀየር ያደረጋቸው ለውጦች አሉ፡፡
Comments