የተዘረፉ ቅርሶንችን፣ ህግ ጠቅሶ ማስረጃ አሳይቶ ወደ ሀገር እንዲመጡ ማስደረግ እንደሚቸግር  ተነግሯል
TRACK

የተዘረፉ ቅርሶንችን፣ ህግ ጠቅሶ ማስረጃ አሳይቶ ወደ ሀገር እንዲመጡ ማስደረግ እንደሚቸግር ተነግሯል

Avatar

ታህሳስ 11፣2017

ከዓመታት ጥረት በኋላ ኢትዮጵያ ጥንት ከተወሰዱባት ቅርሶች ጥቂቱ ሊመለሱላት ቢችሉም ዛሬም አብዛኞቹ በተለያዩ የአዉሮፓ ሀገሮች ይገኛሉ፡፡

በወራሪዎች አማካኝነት ተዘርፈዉ በየሙዚየሙ የተቀመጡ የሀገር ቅረሶች እንዲመለሱ የተለያዩ ትረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

በጦርነት ሰበብ በአሳሾች፣ በጎብኚዎች፣ በተመራማሪዎች የተለያዩ መሪዎች በስጦታና በስርቆት ብዙ ቅርሶች ወደ ውጪ ከተወሰዱ ከዓመታት በኋላ ነበር፣ የማስመለሱ ተግባር የተጀመረዉ፡፡

ቅርሶች አንዴ ከሀገር ከወጡ ለማስመለስ በርካታ ጥረትን የሚጠይቅ እንደሆነ የሚያነሱት በቅርስ ባለስልጣን የቅርስ ቁጥጥርና ክትትል ዴስክ ሀላፊ ሰብለወንጌል ተክሉ፤ አሁን ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

Comments

Avatar