መስከረም 20፣2017
በወንጀል ህጉ እስካሁን ገደብ አልባ የነበረውን በፖሊስ የሚጠየቀው 14 ቀን የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ገደብ እንዲኖረው ሆኖ ህጉ እየተሻሻለ መሆኑ ተሰማ፡፡
ወንጀል ሰርቷል ተብሎ የተጠረጠረና በህግ ቁጥጥር ስር የዋለ ግለሰብ ሰርቷል ስለ ተባለው ወንጀል ማስረጃ ለማሰባሰብ በሚል መርማሪ ፖሊስ በያዘው ተጠርጣሪ ላይ ምርመራ ለማድረግ ፍርድ ቤትን በተደጋጋሚ የምርመራ ጊዜ ሲጠይቅ ይስተዋላል።
በስራ ላይ ባለው የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ መደበኛው በሚባለው ወንጀል የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ግለሰቡ በፀረ-ሽብር ወንጀል ተከስሶ እንደሆነ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ሊፈቀድ እንደሚችል ያስቀምጣል።
ነባሩ ሕግ ዳኛው የጊዜ ቀጠሮን ያለ ገደብ እንዲሰጥ ይፈቅዳል።
ከ60 ዓመታት በላይ ስራ ላይ የቆየውን የወንጀል ህግ ለማሻሻል በረቂቅ ደረጃ ያለው አዲሱ ህግ ግን 14 ቀን፣ 28 ቀን እየተባለ የሚፈቀደው የጊዜ ቀጠሮ ገደብ እንዲኖረው ያስችላል፡፡
አዲሱ ህግ ምን ምን ያካትታል?
Comments