የእህል ገበያው በምርት እጥረት ፣ የጥራጥሬና አዝዕርት ገበያው በዋጋ መናር ሲታመስ ይታያል፡፡
TRACK

የእህል ገበያው በምርት እጥረት ፣ የጥራጥሬና አዝዕርት ገበያው በዋጋ መናር ሲታመስ ይታያል፡፡

00:00

ታህሳስ 28/2018

ተመርቷል የሚባለው ምርት ወደ ገበያ በፍጥነት እንዳይደርስ የመንገድ መሰረተ ልማት ምቹ አለመሆን፣ ገበያው በህገወጥ ደላሎች መዘወሩና የህብረት ስራ ማህበራት ደካማ መሆን እንደ ምክንያትነት በባለሞያዎች ተነስቷል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት 1.5 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ኢትዮጵያ ውስጥ መመረቱን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

ነገር ግን ዛሬም የእህል ገበያው በምርት እጥረት ፣ የጥራጥሬና አዝዕርት ገበያው በዋጋ መናር ሲታመስ ይታያል፡፡

መንግስት የህብረተሰቡን ሌማት ሙሉ እንዲሆን ለማድረግ ምርትን ለማትረፍረፍ፣ ገበያውን ለማረጋጋት የተለያየ ስራ ቢሰራም መሬት ላይ የታሰበውን ያህል ለውጥ ሲያመጣ አይታይም፡፡

Comments

00:00