00:00
የካቲት 25 2017
የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ባለው ተፅዕኖ አምራች የነበሩና ከራሳቸው አልፈው ከተሜውን ይመግቡ የነበሩ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ገበሬዎች አሁን እጃቸውን ለእርዳታ ዘርግተዋል፡፡
ባለፉት 3 ዓመታት በተለያዩ ክልሎች የተከሰተው ድርቅ ሚሊዮን አርብቶ አደሮችን እና ገበሬዎችን ተረጅ አድርጎ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
አሁንም በምግብ እና በውሃ እጥረት የተነሳ እርዳታ የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው፡፡
ታድያ ችግሩ ያለባቸው ክልሎች ለመጪው ጊዜም መሰል አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል ያስችል ዘንድ ምን እየሰሩ ይሆን?
በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በስድስት ወረዳዎች በተከሰተ ከባድ ድርቅ ከመቶ ሺህ በላይ ሰዎች እርዳታ ጠባቂና የምግብ ድጋፍ የሚሹ መሆናቸው በተደጋጋሚ ተነግሯል፡፡
Comments
00:00