ላለፉት ሁለት ዓመታት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች  ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲማሩ ሊደረግ ነው ተባለ
TRACK

ላለፉት ሁለት ዓመታት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲማሩ ሊደረግ ነው ተባለ

Avatar

ነሐሴ 21፣2016

ላለፉት ሁለት ዓመታት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍጫቻ ቋንቋ ብቻ ሲማሩ የነበረ ቢሆንም ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እንዲማሩ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡

በ2017 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ባሉ የግልም ሆነ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የእንግሊዘኛ ትምህርት እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡

በ2015 ዓ.ም ወደ ትግበራ የገባው አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ህፃናት ወይም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ብቻ እንዲማሩ የሚያዝ መሆኑ ይታወቃል፡፡

አሁን ግን በመጭው የትምህርት ዘመን ህፃናት ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መማር እንደሚጀምሩ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት አዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ባዘጋጀው 31ኛውን ጉባኤ ላይ ነው።

በጉባኤውም የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ(ፕ/ር)ን ጨምሮ ሌሎችም የዘርፉ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

Comments

Avatar