00:00
ህዳር 6፣ 2017
በኢትዮጵያ ቁጥሩ እየበረከተ ከመጣው ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ውስጥ በስኳር በሽታ ሰዎች ላይ የሚሰደርሰው ጫና እየበረታ ነው ተባለ፡፡
የዓይነት አንድ ወይም (Type One Diabetic) በብዛት የሚያዙት ታዳጊዎች በመሆናቸውም ወላጆች ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ እየሰራሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ የስኳር ህመም ማህበር ተናግሯል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታሰበውን የስኳር ህመም ቀን የተመለከተ አውደጥናት በአዲስ አበባ ተካሄዷል፡፡
የስኳር ህመም ስርጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁጥሩ እየሰፋ መምጣቱንና በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ላይ በስኳር ህመም የሚያዙ ሰዎች ብዛት እየጨመረ መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር ፕሬዝዳንትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌና የስኳር ሃኪም የሆኑት ጌታሁን ታረቀኝ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡
ህመሙ ከሚያደርሰው ጫና ውሰጥ የተወሰነውን ለመቀነስ ማህበሩ በተለይ በአይነት አንድ ስኳር ለተያዙ ታዳጊዎች የተለያየ ድጋፍ እያደረገ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ድጋፉ ለሌሎችም እንዲዳረስ ማህበሩ በጋራ ከሚሰራባቸው ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን እያገዘ ነው ተብሏል፡፡
የስኳር ህመም ሲነሳ የመድሃኒት አቅርቦት ጉዳይ ብዙ ጊዜ ጥያቄ የሚነሳበት በመሆኑ የኢንሱሊንና ሌሎች መድሃኒቶችን በተመለከተ ሸገር የጠየቃቸው የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ንጉሴ አገልግሎቱ ለመጪዎቹ 9 ወራት ድረስ የሚሆን በቂ የመድሃኒት ክምችት እንዳለው ነግረውናል፡፡
Comments
00:00