ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት አቶሚክ ኢነርጂን ለሰላማዊ መንገድ ለመጠቀም ከሩሲያው የስቴት ኑክሌር ኤጀንሲ ሮሳቶም ጋር የተፈራረመችው ስምምነት ምን ላይ ደርሷል?
TRACK

ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት አቶሚክ ኢነርጂን ለሰላማዊ መንገድ ለመጠቀም ከሩሲያው የስቴት ኑክሌር ኤጀንሲ ሮሳቶም ጋር የተፈራረመችው ስምምነት ምን ላይ ደርሷል?

Avatar

ኢትዮጵያ በ2017 እንደ ጎርጎሮሲያኑ የዘመን አቆጣጠር አቶሚክ ኢነርጂን ለሰላማዊ መንገድ ለመጠቀም ከሩሲያው የስቴት ኑክሌር ኤጀንሲ ሮሳቶም ጋር ስምምነት ተፈራርማ ነበር፡፡

ከዚህ ስምምነት በኋላም ከዚህ ተቋም ጋር የአቶሚክ ኢነርጂን ለሰላማዊ ለማዋል በተለይም ለምርምር እና ለሃይል ኢትዮጵያ ራሷን እንድትችል የሚያደርጋት የተለያዩ ስምምነት የተፈራረመች ቢሆን እስካሁን ወደ መሬት ወርዶ የታየ ስራ ግን የለም፡፡

በቅርቡም ሀገሪቱ ኑክሌር ቴክኖሎጂ ለሰላማዊ መንገድ ለማዋል ያሰበችውን ውጥን ለማሳካት የሚያስችላት ሌላ ስምምነት ከሩሲያ ፌደሬሽን ጋር በ2019 እንደ ጎርጎሮሲያኑ የዘመን አቆጣጠር መፈራረማም ይታወሳል።

ታዲያ ኢትዮጵያ ከሩሲያው መንግስት ጋር የተፈራረመቺው ስምምነት አሁን ምን ላይ ነው ብለን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን ጠይቀናል፡፡

በሚኒስቴሩ የቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር መሪ ስራ አስፈፃሚ ተክለማርያም ተሰማ(ዶ/ር) ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

ቴክኖሎጂውን በፍጥነት ወደ ስራ ለማስገባት የፋይናንስ አቅም ችግር ሊሆንብን ይችላል የሚል ስጋት አለብን መንግስት ከቻለ አሁን ካልቻለ ግን መጪው ትውልድ እንዲያሳካዉ ነው ጥረቱ በማለት ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ኢትዮጵያ ይህንን ቴክኖሎጂ ማስተዳደርና በሚገባ መጠቀም እንድትች ለማድረግ አሁን የሰው ሃይል ማብቃት ላይ በሚገባ እየሰራ ነው ብለዋል ዶክተር ተክለማርያም፡፡

አሁን ላይ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ባህርዳር ዩንቨርስቲ ስርዓተ ትምህር�� ቀርፀዋል ሲሉ ነግረውናል፡፡

ነገር ግን ተማሪዎችን በተግባር ለማስተማር የሚያስችላቸው ላብራቶሪ አለመኖሩ ሌላው ችግር መሆኑን አንስተዋል፡፡

Comments

Avatar