ሰኔ 11 2017
ኢትዮጵያ በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን መብት ለማስከበር የተለያዩ አለም አቀፍ ስምምነቶችን አድርጋለች፡፡
ተፈናቃዮች በመጠለያ ጣቢያ መቆየት የሚችሉት 6 ወር ብቻ እንደሆነ ኢትዮጵያ በተቀበለችው የካምፓላው ስምምነት ያስገድዳል፡፡
በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ሲኖሩ የዕለት እርዳታ የማግኘትና ማንኛውንም ሰብአዊም ይሁን ዲሞክራሲያዊ መብታቸው መጠበቅ እንዳለበት ያዛል፡፡
ይሁንና ኢትዮጵያ ከዚህ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን በተመለከተ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር አዋጅ ማፅደቋም ይታወሳል፡፡
ሆኖም አዋጁ ቢጸድቅም በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ስላልወጣ ስለ አዋጁ ብዙ ማለት ባይቻልም ተፈናቃዮችን መልሶ ከማቋቋም ጋር ተያይዞና ችግርንም በራስ አቅም ከመመለስ አኳያ መንግስት ሊተገብራቸው የሚችሉ ስራዎች በህጉ መደንገጋቸውን ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው አቶ ጥጋብ ደሳለኝ አስታውሰዋል::
Comments