የጉራጌ ዞን በዘንድሮው የመስቀል በዓል  790,000  ጎብኝዎችን በማስተናገድ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ አግኝቻለሁ አለ
TRACK

የጉራጌ ዞን በዘንድሮው የመስቀል በዓል 790,000 ጎብኝዎችን በማስተናገድ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ አግኝቻለሁ አለ

Avatar

መስከረም 22፣2017

የመስቀል በአል በሰፊው የሚከበርበት የጉራጌ ዞን በዘንድሮው በዓል ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር 790,000 ጎብኝዎችን በማስተናገድ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ አግኝቻለሁ አለ፡፡

በዚህም በዘንድሮው የመስቀል በአል 119 ሚሊየን ብር ገደማ ተገኝቷል ያለው የዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ በዞኑ ከተዘጋጁ ገበያዎች በቀረቡ ምርቶች እና አገልግሎቶች የተሰበሰበ ነው ብሏል፡፡

በቀደሙት ዓመታት ተጓዦች በመንገዳቸው የሚያጋጥሟቸው ችግሮች እንደነበሩም የተነገረ ሲሆን ዘንድሮው ከቀናት በፊት በተከበረው የመስቀል በዓል ግን ወደ ዞኑ የሚመጡ ጎብኙዎች እንዳለፉት ዓመታት ችግሮች እንዳያጋጥማቸው አስቀድሞ ስራዎች ተሰርተዋል ተብሏል፡፡

Comments

Avatar