ሰኔ 9 2017
በጉዲፈቻ ልጅ ለሚያሳድጉ ወላጆች የወሊድ ፈቃድ መብት እንደሚሰጣቸው ስለ እናት በጎ አድራጎት ድርጅት ጠየቀ።
ድርጅቱ ይህንን ጥያቄ ያቀረበው በዛሬው እለት ታስቦ የሚውለውን የአፍሪካ የህፃናት ቀንን አስመልክቶ በትላንትናው እለት በካሄደው ፕሮግራም ነው።
ስለ እናት በጎ አድራጎት ድርጅት ላለፉት 23 ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች እና አሁን ላይ ደግሞ በአዲስ አበባ እና ሻሸመኔ ከተማ ላይ ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያት ላጡ ህጻናት እና አቅመ ደካማ ቤተሰቦች እየደገ እንደሚገኝ ስራ አስኪያጁ አቶ ያሬድ አብዱ አስረድተዋል።
Comments