በአዲስ አበባ አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ ቢጠናቀቅም አጀንዳዎችን መቀበል እንደሚቀጥል ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ
TRACK

በአዲስ አበባ አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ ቢጠናቀቅም አጀንዳዎችን መቀበል እንደሚቀጥል ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ

00:00

ግንቦት 28፣2016

በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው አጀንዳ የማሰባሰብ መድረክ ቢጠናቀቅም አጀንዳዎችን መቀበል እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ።

በአዲስ አበባ አጀንዳ አለን፤ ሊመከርበት ይገባል የሚሉት አጀንዳ ያላቸው ሁሉ ወደ ኮሚሽኑ በመምጣት ማቅረብ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለሸገር አስረድቷል።

አሁንም ቢሆን በተናጠልም ይሁን በቡድን የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ይዞ ወደ ኮሚሽኑ በአካል በመምጣትም ይሁን በኢሜል በመላክ ማስያዝ እንደሚቻል ኮሚሽነር አምባዬ ኡጋቶ ጠቁመዋል፡፡

ምንታምር ፀጋው

Comments

00:00