00:00
ህዳር 24፣2017
ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከምትልካቸው ምርቶቿ ቡና ቀዳሚውን ሥፍራ ሲይዝ ከገብያ መዳረሻዎቹ መካከል አሜርካ፣ ጃፓን፣ ቤልጂየም፣ ሳውዲ አረብያ እና ጀርመን በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።
በተለይ ደግሞ ቡናን በመልሶ መላክ(Re Export) ንግድ የምትታወቀው ጀርመን እንደ ኢትዮጵያን ከመሳሰሉ አምራች ሀገራት ቡናን ከገዛች በኋላ አጥባ፣ ቆልታ፣ ፈጭታና አሽጋ መልሳ ለዓለም ገበያ በማቅረብ ትታወቃለች።
አውሮፓዊቷ ሀገር የገዛችውን ቡና አቀነባብራ እና ዕሴት ጨምራ መልሳ ወደ ውጪ ሀገር በመላክ ብቻ በዓመት እስከ 6 ቢሊየን ዶላር ወደ ካዝናዋ እንደሚገባ ይነገራል።
በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር የአፍሪካ ቡና አምራች ሀገራት፣ ቡናን ወደ ውጪ በመላክ የሚያገኙት ገቢ በጠቅላላ ተደምሮ እንኳን ትርፋቸው ቡና ከማታበቅለው ጀርመን ያነሰ እንደሆነ የዓለም አቀፉ የቡና ላኪዎች ማህበር (ICO) መረጃ ያሳያል።
ጀርመን እና መሰሎቿ አንድ ፍሬ ቡና ሳይተክሉ ዕሴት ጨምሮ በመሸጥ ብቻ በረብጣ ዶላር ኪሳቸውን መሙላት ከቻሉ፣ ቡና አምራቿ ኢትዮጵያስ በጥሬው ከመላክ ይልቅ ዕሴት ጨምሮ የመሸጡን ነገር ብታስብበት ስንል ባለሞያ ጠየቅን።
Comments
00:00
Before this idea, if you could share with us the prehistory of Abol, Tona and Beraka.