ለመሆኑ ኢትዮጵያ ከጂቡቲ ወደብ በተጨማሪ አማራጭ ወደቦችን ማፈላለጓ የሚያመጣላት ጥቅም ምን ይሆን?
TRACK

ለመሆኑ ኢትዮጵያ ከጂቡቲ ወደብ በተጨማሪ አማራጭ ወደቦችን ማፈላለጓ የሚያመጣላት ጥቅም ምን ይሆን?

00:00

መስከረም 9፣2017

ኢትዮጵያ ከ5 ዓመት በፊት ‘’የሎጂስቲክስ ስትራቴጂ’’ የተሰኘ ሰነድ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ማጸደቋ ተነግሯል፡፡

በዚህ ሰነድም ኢትዮጵያ እንዴት አማራጭ ወደቦችን መጠቀም እንደምትችል ጭምር የያዘ መሆኑን ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡

የጂቡቲ፣ የላሙ፣ የፖርት ሱዳንን እንዲሁም ፖለቲካው ከተረጋጋ ደግሞ የአሰብ እና ምጽዋን ጭምሮ ሌሎች አማራጭ ወደቦችን ምን ያክል እንጠቀም የሚል ሰነድ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሎጂስቲክስ መምህር የሆኑት ማቲዮስ ኢንሰርሙ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡

ኢትዮጵያ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው የወጪ እና ገቢ ንግዷ በጂቡቲ ወደብ ላይ የተመሰረተ እንደሆነም ይናገራሉ፡፡

ለመሆኑ ኢትዮጵያ ከጂቡቲ ወደብ በተጨማሪ አማራጭ ወደቦችን ማፈላለጓ የሚያመጣላት ጥቅም ምን ይሆን?

ለገበሬው፣ ለነጋዴው፣ ለአስመጪው ለላኪው ለገዢው እና ለሻጩስ ጥቅሙ ምን ይሆን?

ያሬድ እንዳሻው

Comments

00:00