ጥቅምት 19፣2017
ዘንድሮ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ እየተሰበሰበ ያለው ገቢ የመጨረሻው ሊሆን እንደሚችል ገቢ አሰባሳቢው ፅህፈት ቤት ተናገረ፡፡
ግንባታው ከ97 በመቶ በላይ እንደደረሰ የሚነገርለት ህዳሴ ግድብ እዚህ እስከሚደርስ ድረስ የአጠቃላይ ወጪው 10 በመቶ ከህዝቡ እየተሰበሰበ ላለፉት 14 ዓመታት ሲገነባ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
በተያዘው ዓመትም የመጨረሻ የተባለውን ገቢ እየሰበሰብኩ ነው ያለው ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤቱ ምናልባት በ2018 ዓመትም የግንባታው የተወሰኑ ስራዎች የሚቀጥሉ ከሆነ እኔም ስራዬን እቀጥላለሁ ብሏል፡፡
የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የፐብሊክ ዲፕሎማሲና የህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚው አቶ ሰለሞን ዳኜ በሶስት ወራት ውስጥ ከህዝቡ ከተሰበሰበው 271 ሚሊዮን ብር ውስጥ 246 ሚሊዮን ብሩ ከሃገር ውስጥ የተሰበሰበ ሲሆን ቀሪው 25 ሚሊዮን ብር ከውጭ የተሰበሰበ እንደሆነ ነግረውናል፡፡
ለግድቡ ከሚሰበሰበው ገቢ ውስጥ አብዛኛው ከሃገር ቤት ሆኖ መቀጠሉን ከሩብ ዓመቱ ሪፖርት ተመልክተናል፡፡
ባለፈው ዓመት 2016 ዓ.ም እንዲሁ ከተሰበሰበው 1.7 ቢሊዮን ብር ከውጭ የተሰበሰበው 17 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው፡፡
Comments