ህዳር 6፣ 2017
አክሱም ሰላም ከወረደ ሁለት ዓመታት ቢያስቆጥርም፤ የሚታሰበውን ያህል ቱሪስቶችን ሊጎበኟት አለመቻላቸው ተነገረ፡፡
የበርካታ ጥንታዊ ቅርስ መገኛ የሆነችው አክሱም ከሰሜኑ ጦርነት ቁዘማ መላቀቋን ያነጋገርናቸው የከተማው ነዋሪዎች ያስረዳሉ፡፡
ባለፉት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረው ጦርነት ምክንያት የቱሪዝም እንቅስቃሴ አክሱም ከተማ ውስጥ ተቋርጦ እንደነበር የነገሩን እነዚህ ነዋሪዎች አሁንም አክሱም ውስጥ ሰላም ቢሰፍንም በሚፈለገው ጎብኚ እየመጣ አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡
Comments