ግሎባል ቁጠባና ብድር የህብረት ስራ ማህበር 30 በመቶ ለቆጠቡ አባላቶቼ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ላስረክብ ነው አለ፡፡
TRACK

ግሎባል ቁጠባና ብድር የህብረት ስራ ማህበር 30 በመቶ ለቆጠቡ አባላቶቼ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ላስረክብ ነው አለ፡፡

Avatar

ጥቅምት 5፣2017

ግሎባል ቁጠባና ብድር የህብረት ስራ ማህበር 30 በመቶ ለቆጠቡ አባላቶቼ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ላስረክብ ነው አለ፡፡

ባለፈው 2016 ዓመት በሁለት ዙር ለ29 አባላቱ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ማስረከቡን የሚናገረው ማህበሩ በያዝነው የጥቅምት ወር መጨረሻ ለተጨማሪ 32 አባላቱ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማስረከብ ህጋዊ ሂደቶችን እያጠናቀቀ መሆኑን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ ተናግሯል፡፡

የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ሞላ ባዘዘው የተዘጋጀው የኤሌክትሪክ መኪና ዋጋው 4ሚሊዮን እንደሆነና መኪኖቹን የሚረከቡት የዋጋውን 30 በመቶ ማለትም 1.2 ሚሊዮን ብሩን ለቆጠቡ አባላቱ እንደሆኑ ነግረውናል፡፡

ኢትዮጵያ ከነዳጅ ይልቅ ፊቷን በኤልክትሪክ ወደሚሰሩ መኪኖች እያዞረች መሆኑን ተከትሎ እንደማህበር ከያዝነው ዓመታዊ እቅድ ከ80 በመቶ በላዩን ገንዘብ ለኤሌክትሪክ መኪና ብድር እየሰጠን ነው ያሉት አቶ ሞላ የኤሌክትሪክ መኪኖች በቻርጅ የሚሰሩ እንደመሆናቸውና አሁን ባለው ሁኔታ በየቦታው ይህ ባለመኖሩ ማህበሩ በራሱ የቻርጅ ማድረጊያ ቦታ እያመቻቸ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

Comments

Avatar