በተለያየ ጊዜ የንፁሃን ዜጎች አፈና እና ዕገታ ከሚፈፀምባቸው አካባቢዎች አንዱ የሆነው የኦሮሚያ ክልል ድርጊቱን ለማስቆም እርምጃዎችን እየወሰድኩ ነው ብሏል
TRACK

በተለያየ ጊዜ የንፁሃን ዜጎች አፈና እና ዕገታ ከሚፈፀምባቸው አካባቢዎች አንዱ የሆነው የኦሮሚያ ክልል ድርጊቱን ለማስቆም እርምጃዎችን እየወሰድኩ ነው ብሏል

00:00

ሐምሌ 3፣ 2016

በተለያየ ጊዜ የንፁሃን ዜጎች አፈና እና ዕገታ ከሚፈፀምባቸው አካባቢዎች አንዱ የሆነው የኦሮሚያ ክልል ድርጊቱን ለማስቆም የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰድኩ ነው ብሏል።

ክልሉ እንዳለው በዚህ አይነቱ ተግባር የተሰማሩ ሰዎች ከጥፋት ተግባራቸው ታቅበው ወደ ሠላማዊ ኑሮ እንዲመለሱ ሁኔታዎችን እያመቻቸ ነው፤ እምቢ ባሉት ላይ ደግሞ የሃይል እርምጃ እየተወሰደባቸው ይገኛል።

በሌላ በኩል ከቀናት በፊት ከታገቱ 167 የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ነጻ መውጣታቸውን ክልሉ ይፋ አድርጓል።

በኢትዮጵያ የሰዎችን አፈና እና ዕገታ የተመለከቱ ዜናዎች በየጊዜው በተደጋጋሚ እየተሰሙ ነው፡፡

Comments

00:00