በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ንረት በግብረ ሰናይ ድርጅቶች በሚከውኑ ፕሮጀክቶች ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑ ተነግሯል
TRACK

በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ንረት በግብረ ሰናይ ድርጅቶች በሚከውኑ ፕሮጀክቶች ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑ ተነግሯል

00:00

የካቲት 21 2017

በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ንረት በግብረ ሰናይ ድርጅቶች በሚከውኑ ፕሮጀክቶች ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ባሉ 5 ወረዳዎች በ56 ቀበሌዎች በጀርመን መንግስት በተገኘ የ8.8 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ 163 የውሃ ፕሮጀክቶች ተሰርተዋል፡፡

ጀርመን አግሮ አክሽን ከሌሎችም አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ከ2008 ዓ.ም እስከ 2017 ዓ.ም አጋማሽ በከወነው በዚህ የውሃ ፕሮጀክት 163 የውሃ ፕሮጀክቶችን በመስራት የአካባቢውን የውሃ አቅርቦት ወደ 45 በመቶ ማድረሱን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ አለማየሁ ወርቁ ነግረውናል፡፡

በፕሮጀክቱ ትግበራ ወቅት በተለይ ካለፈው ዓመት መጨረሻ ጀምሮ የብር የመግዛት አቅም በመዳከሙ የመጣው የዋጋ ንረት የፀጥታ ችግሮችና ውሃ የማይገኝባቸው የመከኑ ግድጓዶች መኖር እንቅፋት እንደነበሩ አንስተዋል፡፡

የአማራ ክልል የውሃ ኢነርጂ ቢሮ በበኩል ለፕሮጀክቱ ትግበራ በየአዓመቱ ከ6 እስከ 10 ሚሊዮን ብር በመመደብ ሲያግዝ መቆየቱን የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው ነግረውናል፡፡

Comments

00:00