TRACK
''በኢትዮጵያ ካሉ 30 የግል ባንኮች ውስጥ ሀብታቸው ከ1 ቢሊዮን ዶላር የሚያልፈው አራቱ ብቻ ናቸው'' የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው
ታህሳስ 18፣2017
በኢትዮጵያ ካሉ 30 የግል ባንኮች ውስጥ ሀብታቸው ከ1 ቢሊዮን ዶላር የሚያልፈው አራቱ ብቻ ናቸው ይላሉ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረዮሃንስ፡፡
የኢትዮጵያ የግል ባንኮች መንግስት ለግሉ ዘርፍ ፕሮጀክት ግንባታ ገንዘብ ልበደር ቢል እንኳን የማበደር አቅም እንደማይኖራቸው ያስረዱት የፕራግማ ካፒታል መስራች እና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የፋይናንስ ባለሙያው አቶ መርዕድ ለዚህም የውጭ ባንኮች እንዲገቡ የሚፈቅደው አዋጅ መጽደቁ የዘገየ እንጂ የፈጠነ ውሳኔ አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ፡፡
ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ የባንክ መስኩን ከውጭ ባንክ ጠብቃ ማቆየቷ ጥቅሙ የሃገር ሳይሆን የ450 ሺህ የባንክ የአክሲዮን ባለቤቶች ነው ይላሉ፡፡
ለዚህም ከ450 ሺህ ባላአክሲዮኖች ጥቅም የሃገር ጥቅም ስለሚበልጥ የውጭ ባንኮች እንዲገቡ የሚፈቅደው አዋጅ ተገቢ ነው ሲሉ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረ ዮሃንስ አስረድተዋል፡፡
ባንኮች ባላቸው ሃብት መጠን ነው ማበደርም ሆነ ለሃገርም መጥቀም የሚችሉት የሚሉት ባለሙያው ለምሳሌ የአገሪቱ ትልቁ ባንክ ሀብቱ 1.4 ትሪሊዮን ብር ነው ከዚህ ባንክ 3 መቶ ቢሊዮን ብር መበደር ይቻላል ምክኒያቱም ሃብቱ ትልቅ ነው ብለዋል፡፡
Comments