TRACK
በትግራይ አጀንዳ ማሰባሰብ እንዴት ይከወን በሚለው ጉዳይ ከክልሉ ጊዜዊ አስተዳደር ጋር ተደጋጋሚ ውይይት እያደረገ መሆኑን የምክክር ኮሚሽን ተናግሯል
ሰኔ 11 2017
በትግራይ ክልል ለሃገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ለማሰባሰብ ስራዎች ተጀምረዋል፡፡
በክልሉ አጀንዳ ማሰባሰብ እንዴት ይከወን በሚለው ጉዳይ ዙሪያ ከክልሉ ጊዜዊ አስተዳደር ጋር ተደጋጋሚ ውይይት እያደረገ መሆኑን የብሄራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናግሯል፡፡
ከትግራይ ክልል በስተቀር በአዲስ አበባንና ድሬደዋ ከተማ አስተዳድሮች እንዲሁም በሁሉም ክልሎች ሊመከርባቸው ይገባል የተባሉ አጀንዳዎችን ሲያሰባስብ የቆየው ኮሚሽኑ ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ አጀንዳዎችን ለማሰባሰብ የሚያስችሉትን ውይይቶች እያደረገ መሆኑን ነግሮናል፡፡
በክልሉ አሁን በስራ ካለው ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በክልሉ ካሉት 4ቱም ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከምሁራን፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በየደረጃው እየተደረጉ ባሉ ውይይቶች ስራው እንዴት ይሰራ በሚለው ጉዳይ ዙሪያ እየተነጋገሩ መሆኑን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡
Comments