00:00
የካቲት 17/2018
በጋምቤላ ክልል ናፍጣ ከገበያው ዋጋ በላይ በሊትር እስከ 280 ብር እየተሸጠ ነው ሲሉ በክልሉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡
የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ከአልሚዎቹ እየተነሳ ስላለው ቅሬታ አላውቅም ብሏል፡፡
ይህ የናፍጣ የሽያጭ በህገወጥ መንገድ ሳይሆን በግላጭ በማደያዎች እየተፈፀመ እንደሆነም ሰምተናል።
በነዳጅ መጨመር ምክንያትም ከ75% በላይ የሚሆን የእርሻ መሬት ፆም አዳሪ ሆኖ እንደሚከርምም አልሚዎቹ ስጋታቸውን ነግረውናል። ስራ ያቆሙ እንዳሉም ሰምተናል።
በዚህ ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚዎች በታሪፉ የሚቀርበውን ነዳጅ የክልሉ ንግድ ቢሮ ከደላሎች ጋር ተመሳጥሮ እየተጠቀሙበት ነውም ብለውናል።
የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ በበኩሉ አንድ ነዳጅ በ134 ብር ከ 79 ሳንቲም እንደሚሸጥ እንጂ እስከ 280 ብር እንደሚሸጥ አላውቅም ብሏል ።
የጋምቤላ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ ኩአንግ ኩላንግ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን በሚመለከት የመጣ ቅሬታ የለም ብለዋል።
በኢንቨስትመንት ቢሮ በኩል የመጡ ቅሬታዎች ግን አሉ፥እሱም የነዳጅ አቅርቦትን የተመለከተ ነው ለተወሰኑት አቅርበናል ብለዋል ።
Comments
00:00