ዘርፉ በክልሉ ያላደገበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠይቀናል
TRACK

ዘርፉ በክልሉ ያላደገበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠይቀናል

Avatar

ሰኔ 20፣ 2016

አጠቃላይ ካፒታላቸው ከስድስት መቶ ሺህ እስከ አስር ሚሊየን ብር የሆኑ እና ከስድስት እስከ ሃምሳ የሚሆኑ ሰዎችን፤ በስራቸው ይዘው የሚያሰሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች አነስተኛ በሚል ይጠራሉ።

ካፒታላቸው ከአስር ሚሊየን እስከ ዘጠና ሚሊየን ብር የሆኑት እና ከሃምሳ አንድ እስከ መቶ ሰዎችን፤ ይዘው የሚያሰሩት ደግሞ መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች በሚል ይታወቃሉ።

እንደዚህ አይነት 25,200 አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ እንዳሉ ሠምተናል።

የእነዚህ ኢንዱስትሪዎች ስርጭት በክልሎች የተመጣጠነ እንዳልሆነ ግን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት፤
የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አሸናፊ መለሠ ተናግረዋል።

ለአብነትም በአፋር ክልል ስለሚገኙ አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ብዛት ከአንድ መቶ አይበልጡም ብለዋል።

ዘርፉ በክልሉ ስላላደገበት ምክንያት ምን እንደሆነ ጠይቀናል፡፡

Comments

Avatar