ሐምሌ 24፣2016
በአማራ ክልል ያለው የሰላም እጦት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራሉ መንግስት ሁሉንም አማራጭ እንዲጠቀሙ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ጠየቁ፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በበኩላቸው ችግሩን በውይይት እና በድርድር ለመፍታት አምነንበት እየሰራንበት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት አሁን ላይ በክልሉ ባለው ግጭት ህዝቡ ለከፋ ችግር መጋለጡ እና የተጀመሩ የመሰረተ ልማቶች መጓተታቸውን አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በነበረው የሰሜኑ ጦርነት አገግሞ ወደ ልማቱ ቢመለስም አሁንም ሌላ ግጭት ውስጥ በመግባት የተሰሩ የመሰረተ ልማቶች መውደማቸውን የምክር ቤቱ አባላት የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ አንስተዋል፡፡
ማርታ በቀለ
Comments