ኢሰመኮ በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጭ የሚደረግ የሰዎች እስር፣ አፈናና አስገድዶ መሰወር መኖሩን በክትትል ሪፖርቱ ማረጋገጡን በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡
TRACK

ኢሰመኮ በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጭ የሚደረግ የሰዎች እስር፣ አፈናና አስገድዶ መሰወር መኖሩን በክትትል ሪፖርቱ ማረጋገጡን በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡

Avatar

መስከረም 6፣2017

መንግስታዊው የኢትየጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) በኢትዮጵያ ከህግ አግባብ ውጭ የሚደረግ የሰዎች እስር፣አፈናና አስገድዶ መሰወር መኖሩን በክትትል ሪፖርቱ ማረጋገጡን በተደጋጋሚ ይናገራል፡፡

ኮሚሽኑ በተጠናቀቀው ዓመት 2016 ዓ.ም በፖሊስ ጣቢያዎች አደረግኩት ባለው ክትትል በተለይም “በወቅታዊ ሁኔታ” በሚል የሚያዙ ተጠርጣሪዎችን በ48 ሰዓት ውስጥ ወይም በጭራሽ ፍርድ ቤት አለማቅረብ፣ በፍርድ ቤት ነፃ የተባሉ፣ የዋስትና መብታቸው የተጠበቀላቸው እንዲሁም የምርመራ መዝገባቸው በዐቃቤ ሕግ አያስከስስም ተብሎ የተዘጋ ሰዎችን አስሮ ማቆየት፣ በወንጀል ተጠርጣሪዎች ምትክ የቤተሰብ አባላትን ማሰር፣ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በአስተዳደር አካላት፣ በመከላከያ ሰራዊት እና በፖሊስ አባላት ጭምር ሰዎችን ከሕግ ውጭ ማሰር እንዳለ ማረጋገጡን በክትትል ሪፖርቱ አካትቷል፡፡

በአብዛኛው እንዲህ ዓይነቱ እስር ፖለቲካዊ መልክ ያለው ነው ያሉን የደብረ ታቦር ዩንቨርሲቲ የህግ መምህርና ጠበቃው አቶ መሳፍንት አላቸው ናቸው፡፡

በህዝቡ ዘንድ በፖለቲካ ተሳትፏቸው ተለይተው የሚታወቁ፤የማታወቁም ቢሆኑ መንግስት የፖለቲካ ተቀናቃኝ ናቸው የሚላቸው ግለሰቦች እየታደኑ በምሽት ሳይቀር እየታፈኑ ሲወሰዱ መመልከት የተለመደ ሆኗል ይላሉ፡፡

ታዋቂ የሆኑት አንዳንድ ጊዜ ይፈቱ የሚል ዘመቻ ይከፈትላቸዋል፤የማይታወቁት ደግሞ ለዓመታት እስር ቤት ይማቅቃሉ፤ የት እንደታሰሩ ሳይታወቅ፣ክስም ሳይመሰረትባቸው ታስረው ለዓመታት ቆይተው በድንገት በነፃ ይለቀቃሉ ይላሉ፡፡

Comments

Avatar