ጥቅምት 4፣2017
የውጪ ሀገራት ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ከሌሎች ጎብኚዎች ከሰሙት መረጃ ተነስተው እንጂ ሀገሪቱ በሰራችው ማስታወቂያ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማህበር ተናገረ፡፡
ማህበሩ እንዳለው በየጊዜው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቱሪስቶች ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው መረጃ ባለሙያዎቻችን ሲጠይቋቸው አብዛኛዎቹ ስለ ኢትዮጵያ የሚያውቁት ነገር የለም ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ቱሪስት አስጎብኚ ባለሙያዎች ማህበር ዋና ፀሐፊ አቶ አቤል መኮንን አብዛኛዎቹ የውጪ ሀገራት ጎብኚዎቻችን ስለ ኢትዮጵያ መረጃ የሚሰሙት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ከጎበኙ ጓደኞቻቸው አልያም ተጓዦች ነው፡፡
Comments