ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ጅቡቲ በዓመት ከውጪ ሀገራት ከ21 ሚሊዮን ዶላር በሚበልጥ ገንዘብ የዶሮ ስጋና እንቁላል ወደ ሀገራቸው ያስገባሉ ተባለ
TRACK

ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ጅቡቲ በዓመት ከውጪ ሀገራት ከ21 ሚሊዮን ዶላር በሚበልጥ ገንዘብ የዶሮ ስጋና እንቁላል ወደ ሀገራቸው ያስገባሉ ተባለ

Avatar

ሐምሌ 11፣ 2016

ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ጅቡቲ ከፍተኛ የዶሮ ሀብት ባለቤቶች ቢሆኑም በዓመት ከውጪ ሀገራት ከ21 ሚሊዮን ዶላር በሚበልጥ ገንዘብ የዶሮ ስጋና እንቁላል ወደ ሀገራቸው ያስገባሉ ተባለ፡፡

የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት የእንስሳት ሀብትና ገበያ ጥናት ከፍተኛ አማካሪው አመሃ ሰብስቤ ለሸገር እንደተናገሩት በተለይም በኢጋድ አባል ሀገራት ውስጥ ያለው የዶሮ ሀብት ልማትን እንደ አማራጭ የገቢ ምንጭ ለመጠቀም በጋራ መተባበር አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡

የኢትዮጵያ፣ የደቡብ ሱዳን፣ የኬንያ ፣የሶማሊያ እና የጅቡቲ ከፍተኛ ባለሞያዎች የተገኙበት በዶሮ ሀብት ዙሪያ የሚመክር ጉባኤ በአዲስ አበባ ትናንት መከፈቱ ተነግሯል፡፡

Comments

Avatar