በጡት ካንሰር ህመም መያዛቸው በህክምና ከሚረጋገጥ ሰዎች መካከል 60 በመቶዎቹ እንደሚሞቱ ተነገረ፡፡
TRACK

በጡት ካንሰር ህመም መያዛቸው በህክምና ከሚረጋገጥ ሰዎች መካከል 60 በመቶዎቹ እንደሚሞቱ ተነገረ፡፡

Avatar

ግንቦት 1 2017

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በጡት ካንሰር ህመም መያዛቸው በህክምና ከሚረጋገጥ ሰዎች መካከል 60 በመቶዎቹ እንደሚሞቱ ተነገረ፡፡

በሃገሪቱ በየዓመቱ ምን ያህል ሰዎች በጡት ካንሰር ህመም ይጠቃሉ የሚለውን ለማወቅ የተደረገ ጥናት ባይኖርም ከጤና ተቋማት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በየዓመቱ 17 ሺህ ያህል ሰዎች በጡት ካንሰር መያዛቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

ከእነዚህ መካከል 9 ሺህ ያህሉ (60%) ለህልፈት እንደሚዳረጉ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ተናግሯል፡፡

ታማሚዎቹን ለዚህ የሚያበቃቸው ደግሞ አባዛኞቹ ተጠቂዎች ወደ ህመሙ እንዳለ በህክምና ለማረጋገጥ ባለሙያ ጋር የሚቀርቡት ህመሙ ጠንቶ መዳን ወደማይችልበት ደረጃ ከደረሰ በኋላ ስለሆነ ነውም ብሏል፡፡

Comments

Avatar