ጥር 16 2017
በትግራይ ክልል በሕወሃት መካከል የተፈጠረው ክፍፍል ወታደራዊ አገዛዝን በሕዝቡ ላይ እንዲጫን ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲሉ የቀድሞ የህወሃት መስራችና የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ገብሩ አስራት ተናገሩ፡፡
ትናንትና የትግራይ የጦር ሀይሎች አዛዦች የሰጡት መግለጫ ክልሉን ወደ ከፋ የእርስ በርስ ግጭት እንዳይወስደው እሰጋለሁ ብሏል፡፡
በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱ ይነገራል፡፡
የፕሪቶሪያው ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ ስራዎች ቢሰሩም በሰራዊቱ በኩል ግን ከአስተዳደሩ ጋር ያለው ልዩነት ጎልቶ እየወጣ ነው፡፡
Comments