ሰኔ 23 2017
በኢትዮጵያ የሴት ልጅ ግርዛት፣ የህፃናት ያለ እድሜ እና የግዳጅ ጋብቻ ለማስቀረት አሁንም የሚጠበቁ ስራዎች አሉ ተባለ፡፡
በሀገሪቱ እነዚህ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው ስፋቱ ቢቀንስም አሁንም ግን በዚህ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የሚስተጓጎሉ፣ የጤና ጉዳት የሚገጥማቸው ልጃገረዶች አሉ ተብሏል፡፡
በዚሁ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያ የሚሰሩት፤ የኖርዌይ ቸርች ኤይድ ኢትዮጵያና ሴቭ ዘ ቺልድረን ኢንተርናሽናል፤ ከኖርዌይ መንግስት በተገኘ ድጋፍ የሴት ልጅ ግርዛት የህፃናት ያለ እድሜና የግዳጅ ጋብቻ ለማስቀረት የሚተገበር አምስተኛ ዙር ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል፡፡
ከዚህ የቀደም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተመሳሳይ አራት ፕሮጀክቶች መተግበራቸውንና የአምስተኛው መርሃ ግብር በአምስት ክልሎች ላይ የሚሰራው መሆኑን የነገሩን የኖርዌጂያን ቸርች ኤይድ የኢትዮጵያ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ቅድስት በላይነህ ናቸው፡፡
Comments