በግጭት ውስጥ በቆዩ አካባቢዎች የወደሙ ጤና ተቋማት በበቂ ሁኔታ ስላልተቋቋሙ የሚሞቱ እናቶችና ህፃናት ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ
TRACK

በግጭት ውስጥ በቆዩ አካባቢዎች የወደሙ ጤና ተቋማት በበቂ ሁኔታ ስላልተቋቋሙ የሚሞቱ እናቶችና ህፃናት ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ

Avatar

በግጭት ውስጥ በቆዩ አካባቢዎች የወደሙ ጤና ተቋማት በበቂ ሁኔታ መልሰው ስላልተቋቋሙ የሚሞቱ እናቶች እና ህፃናት ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡

በአንዳንድ ክልሎች የሚጣሉ ህፃናት ቁጥርም እንዲሁ ጨምሯል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በእናቶችና ሕፃናት ሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ ለ1 ዓመት ያደረገውን ክትትልና ምርመራ ውጤት በሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

በሪፖርቱ ከተጠቀሱት መካከል የሚከተሉት ነጥቦች ይገኙበታል፡፡

በግጭት ምክንያት የወደሙ የህክምና ተቋማት በበቂ መልሰው ስላልተቋቋሙ እናቶች የወላድ አገልግሎት ለማግኘት ተቸግረዋል፡፡

በአፋር፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልል የሚጣሉ ህፃናት ቁጥር ጨምሯል፡፡

በህፃናት ማሳደጊያዎች ውስጥ በህፃናት ላይ የሚደርሰው የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲስተካከል የተሰጡ ምክረ ሀሳቦች እየተተገበሩ አይደለም፡፡

በአዲስ አበባ በተለያየ ወንጀል ተሳትፈዋል የተባሉ ህፃናት በሚገቡበት የተሃድሶ ማዕከል የሰብአዊ መብት ጥሰት ይደርስባቸዋል፡፡

Comments

Avatar