ህዳር 16፣2017
በተለይ ካውጭ የሚጋቡ ምርቶች ዋጋ ከእለት እለት አልቀመስ ብሏል፡፡
ለዚህ ዋናው መነሻ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ያስከተለው የብር የመግዛት አቅም በእጥፍ መዳከም እንደሆነ ይነገራል፡፡
ለመሆኑ የፖሊሲ ማሻሻያውን ተከትሎ የመጣውን የገበያ ውድነት ህብረተሰቡ ላይ የደቀነውን ጫና ለመቀነስ ሲባል መንግስት ያለፉትን አራት ወራት የተከተላቸው አሰራሮች እንዴት ይታያሉ?
መንግስት የዋጋ ውድነቱ እንዳይባባስ እወስዳለሁ ያላቸው እርምጃዎችስ ለውጥ አምጥተዋል ማለት ይቻላል ወይ? ስንል ባለሞያን ጠይቀናል።
ስለ ጉዳዩ የጠየቅናቸው የምጣኔ ሐብት ባለሞያ መንግስት ገቢውን ለማሳደግ የወሰዳቸው የተለያዩ እርምጃዎች የዋጋ ወድነቱን አባብሰውታል ብለዋል፡፡
Comments