ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያደርጓቸው ጥናቶችና ምርምሮች ቅድሚያ በሚሰጣቸው የኢትዮጵያ ችግሮች ላይ ያተኮሩ አይደለም
TRACK

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያደርጓቸው ጥናቶችና ምርምሮች ቅድሚያ በሚሰጣቸው የኢትዮጵያ ችግሮች ላይ ያተኮሩ አይደለም

Avatar

ነሐሴ 24፣2016

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያደርጓቸው ጥናቶችና ምርምሮች ቅድሚያ በሚሰጣቸው የኢትዮጵያ ችግሮች ላይ ያተኮሩ አይደለም፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር እንደሚለው ተቋማቱ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ችግሮች ላይ የማያተኩሩት የበጀት እጥረትና ትኩረት የመስጠት ችግር ስላለባቸው ነው፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘረፍ የምርምርና ስርፀት ዴስክ ኃላፊ ዶክተር ሰራዊት ሃንዲሶ እንዳሉት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥናትና ምርምር ለማድረግ በጀት ይመድባሉ፡፡

ነገር ግን ጥናቶቹ ሀገሪቱን ወጥረው ይዘውኛል የምትላቸውን ችግሮች በመፍታት ላይ ያተኮሩ አለመሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት ትምህርት ሚኒስቴር ጥናትና ምርምሮች የተሻለ በጀት እንዲያገኙ ለማድረግና መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ እየተሰራ ነው ይላሉ፡፡

Comments

Avatar