የውጭ ሀገር ፓስፖርት ያላችሁ ሁሉ የሆቴል አገልግሎት የሚያገኙት በውጭ ምንዛሬ እንዲሆን የሚያዘው የቆየ መመሪያ ቁጥጥሩ ሊበረታ ይገባል ተባለ
TRACK

የውጭ ሀገር ፓስፖርት ያላችሁ ሁሉ የሆቴል አገልግሎት የሚያገኙት በውጭ ምንዛሬ እንዲሆን የሚያዘው የቆየ መመሪያ ቁጥጥሩ ሊበረታ ይገባል ተባለ

Avatar

ሐምሌ 11፣ 2016

የውጭ ሀገር ፓስፖርት ያላችሁ ሁሉ የሆቴል አገልግሎት የሚያገኙት በውጭ ምንዛሬ እንዲሆን የሚያዘው የቆየ መመሪያ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን የሚያስታግስ በመሆኑ ቁጥጥሩ ሊበረታ ይገባል ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ካለፈው ሐምሌ 2 ጀምሮ የውጭ አገር ዜጎችን የትኬት አገልግሎት የሚያገኙት በውጭ ምንዛሬ ብቻ ይሆናል ብሏል፡፡

• ሆቴሎች የውጭ ፓስፖርት የያዘን ግለሰብ በብር ማስተናገድ የሚችሉት ይዞት የመጣውን የውጭ ምንዛሬ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ በህጋዊ መንገድ ወደ ብር የመነዘረበትን ተመጣጣኝ ሰነድ ካገኙ ብቻ ይሆናል፡፡

• ኢትዮጵያውያን ወደ ውጭ ለሚያደርጉት በረራ እንደቀድሞው በብር ትኬት መቁረጥ ይችላሉ፡፡

• በኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ ሃገራት አየር መንገዶች ጨምሮ የውጭ ሃገር ዜጎችን (የዲፕሎማቲክ ፈቃድ ያላቸውን ጨምሮ) በውጭ ምንዛሬ ብቻ የትኬት አገልግሎት እንዲሰጡ ይገደዳሉ፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…

ትዕግስት ዘሪሁን

#የሆቴል_አገልግሎት #ፓስፖርት

Website: https://www.shegerfm.com/

Comments

Avatar