በ10 ዓመት ውስጥ 148 ሺህ አውቶሞቢሎችና ከ 4,800 በላይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶች በኢትዮጵያ  እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው  ተባለ
TRACK

በ10 ዓመት ውስጥ 148 ሺህ አውቶሞቢሎችና ከ 4,800 በላይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶች በኢትዮጵያ እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተባለ

00:00

ግንቦት 30፣2016

በአስር ዓመት ውስጥ 148 ሺህ አውቶሞቢሎችና ከ 4,800 በላይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶብሶች በኢትዮጵያ እንዲኖሩ ለማድረግ እየተሰራ ነው ሲል የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

በኤሌክትሪክ መኪና ማስመጣት ላይ የተሰማሩም፤ የኤሌክትሪክ መኪኖች ተፈላጊት እጨመረ መጥቷል ብለዋል።

መንግስት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ለሚያስገቡና በሀገር ውስጥ ለሚገጣጣጥሙ የታክስ ማበረታቻ ከማድረግም በተጨማሪ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እየሰራ እንደሆነ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አቶ በርኦ ሀሰን ተናግረዋል።

የቻርጅ መሙያ ማዕከላትን በማስፋፋት፣ በጋራዥና ጥገና ዘርፍ፣ በዘርፉ ባለሞያዎችን በማሰልጠን በኩል እገዛ እንደሚያስፈልግ ሚኒስትር ዴኤታው አንስተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው የዓለም ባንክ የትራንስፖርትና ኢነርጂ ቡድንን ባነጋገሩበት ወቅት ከተሽከርካሪዎች የሚለቀቀውን በካይ ጋዝ ለመቀነስ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣ በብዙሃን ትራንስፖርት እና በሞተር አልባ ትራንስፖርት ማስፋፋት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው፣ ለተግባራዊነቱ የአጋር አካላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ንጋቱ ሙሉ ያሰናዳውን በያሬድ እንዳሻው

Comments

00:00