''ካሉ አካል ጉዳተኛ ህፃናት ውስጥ ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት የትምህርት እድል እያገኙ አይደለም'' ኢሰመኮ
TRACK

''ካሉ አካል ጉዳተኛ ህፃናት ውስጥ ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት የትምህርት እድል እያገኙ አይደለም'' ኢሰመኮ

00:00

ታህሳስ 21፣2017

በኢትዮጵያ ካሉ አካል ጉዳተኛ ህፃናት ውስጥ ከ85 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑት የትምህርት እድል እያገኙ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡

ለአካል ጉዳተኞች የመማሪያ ቦታ፣ መምህር የለንም በሚል ትምህርት ቤቶች አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች አይቀበሉም ተብሏል፡፡

የኢሰመኮ የሴቶች፣ ሕፃናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ ወላጆች አካል ጉዳተኛ ሕፃናትን ወደ ትምህርት ቤት ሊያስመዘግቡ ሲሄዱ የግልም ሆነ የመንግስት ትምህርት ቤቶች አንቀበልም ብለው እንደሚመልሷቸው በተለያዩ ጊዜያቶች ወላጆች አቤቱታቸው ለኮሚሽኑ እንደሚያቀርቡ ነግረውናል፡፡

Comments

00:00