00:00
ሰኔ 13 2017
በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን አንደማይፈቅድ የፍትህ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
የፍትህ ሚኒስቴር ይህን የተናገረው ባለፈው ሰኔ 10 ቀን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባጸደቀው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ የቀረበውን አዋጅ ይዘት በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡
መስሪያቤቱ አዋጁን አንዳንዶች የተረዱበት መንገድ ልክ አይደለም ብሏል፡፡
ስለ አዋጁ ማሻሽያ፣ ይዘት እና ምንነት ማብራርያ የሰጡት የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመቆጣጠር ተቋም ያቋቋመችው በ2002 ዓ.ም ነው ብለዋል፡፡
የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል 40 ቀጥታ አባል አገራት አሉት፡፡ እንዲሁም ደግሞ ዘጠኝ ቀጠናዊ አባል ሀገሮች አሉ ተብሏል።
ከአፍሪካም ሶስት የምስራቅ እና ደቡቡን የሚያካትተው 21 አባል ሀገሮችን የያዘው የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካን የያዘው ኢስተርን ነደ ሶውዘርን አፍሪካ አንቲ ላውንድሪ ግሩፕ (eastern and southern africa anti money laundry group) ይባላል፡፡ ኢትዮጵያም ከ21 አባል ሀገራት አንዱ ናት ሲሉ ተናግረዋል፡፡
Comments
00:00