በኢትዮጵያ በየዓመቱ በጡት ካንሰር ከሚያዙ ሴቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ ዘግይተው ወደ ህክምና የሚሄዱ በመሆኑ ህይወታቸውን ያጣሉ ተባለ
TRACK

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በጡት ካንሰር ከሚያዙ ሴቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ ዘግይተው ወደ ህክምና የሚሄዱ በመሆኑ ህይወታቸውን ያጣሉ ተባለ

Avatar

ግንቦት 21 2017

በኢትዮጵያ በየአመቱ በጡት ካንሰር ከሚያዙ ሴቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ ዘግይተው ወደ ህክምና የሚሄዱ በመሆኑ ህይወታቸውን ያጣሉ ተባለ፡፡

በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች ቀዳሚ የሆነው የጡት ካንሰር የብዙ ሴቶች ፈተና ሆኗል፤ በገዳይነቱም ቀዳሚ ነው፡፡

ነገር ግን ቀድሞ ከታወቀ እና በጊዜ ከተደረሰበት ታክመው መዳን እንደሚቻል ከህመሙ ያገገሙና በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የካንሰር ቅድመ ጥንቃቄ ላይ የሚሰሩ ሴቶች ይመሰክራሉ፡፡

የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር ህመም ዓይነቶች በቀዳሚነቱ የመጀመሪያ መሆኑን የሚናገሩት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የካንሰር ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶክተር ሙሉጌታ ካሳሁን ናቸው፡፡

የካንሰር ህመም በሰውነት ላይ ከመሰራጨቱ በፊት የተለያዩ ደረጃዎች እንዳሉት የሚናገሩት ዶክተር ሙሉጌታ ህመሙ ቀድሞ ከተደረሰበት ግን መታከም የሚችል ቢሆንም አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ሴቶች መታከም የማይችልበት ደረጃ ላይ ሲደርስ ነው ወደ ህክምና የሚመጡት ይላሉ፡፡

በተለይ በከተሞች ላይ ያለው ጤናማ ያልሆነ ያኗኗር ሥርዓት ለካንሰር መከሰት ምክንያት መሆኑን የሚናገሩት ዶክተር ሙሉጌታ ነገር ግን አብዛኛዎቹ የካንሰር ዓይነቶች ለመታከም ከዘገዩ በኋላ የሚታወቁ መሆናቸው ችግሩን አክብዶታል ይላሉ፡፡

Comments

Avatar