የካቲት 20፣2016
የሽንኩርት፣ የቃሪያ እና የቲማቲም ምርትን ያሳድጋሉ የተባሉ ምርጥ ዘሮች ከኔዘላንድስ ለኢትዮጵያ ገበሬዎች ተሰጡ፡፡
የአትክልት ዘሩን እርዳታ የሚሰጠው ቢ ኤ ኤስ ኤፍ(BASF) የተባለ ድርጅት ሲሆን የኔዘርላንድስ ልማት ድርርጅት ኤስኤንቪ(SNV) እርዳታውን ለገበሬዎች ያደርሳል ተብሏል፡፡
ለገበሬዎች ይሰጣል የተባለው የአትክልት ምርጥ ዘር 291 ሄክታር መሬት ይሸፍናል የተባለ ሲሆን በጦርነትና ድርቅ ውስጥ ያሉ ገበሬዎች ስራቸው እንዲቀጥሉ ያደርጋል ተብሏል፡፡
የቢ ኤ ኤስ ኤፍ የኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቤን ዴፕራቴር እንዳሉት አሁን ለገበሬዎች የሚሰጠው የአትክልት ምርጥ ዘር ገበሬዎቹ እራሳቸው እንዲችሉና የተሻለ ገበያ እንዲገኙ ያግዛል ብለዋል፡፡
የኤስኤንቪ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጁሊ ግርሃም አሁን የሚሠጠው እርዳታ በተለይም ጦርነትና ድርቅ ባለባቸው የአማራ እና ትግራይ ክልል ገበሬዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዕታ መለስ መኮንን እንዳሉት በሁለቱ ክልሎች ውስጥ ድጋፍ የሚደረግላቸው 4 ሺህ ገበሬዎች ተለይተዋል ብለዋል፡፡
ቢ ኤ ኤስ ኤፍ ድጋፍ ያደረገው 800 ኪሎ ግራም ሽንኩርት፣ 666,000 ኪሎ ግራም ቃርያ እና 1.5 ሚልዮን ኪሎ ግራም ቲማቲም መሆኑን ሰምተናል፡፡
በረከት አካሉ
#Ethiopia #ShegerWerewoch #ፆታዊ_ጥቃት #ሽንኩርት
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments